Telegram Group Search
💡ያለፈበት ብቻ ያውቀዋል!!

ትልልቅ ቦታ ላይ የደረሱን ሰዎች ስለ ትናንት ህይወታቸው ስትጠይቃቸው ሁሉም ፊት ላይ ደስተኝነትን አታነብም:: ሁሉም በእምባ እናም በትጋዜ ተሞልተው ይነግሩሀል፣ ከሙቀት ዋሻህ ውስጥ የምትወጣበት፣ከተወዳጅነት አጀብታ ለነፍስህ ፍላጎትና ለህልምህ የምትወርድበት ጥልቁና አስፈሪው የህይወት መንገድህ ነው።

📍ያስፈራል ልብ ያርዳል ነገር ግን ነፍስን ለጥበብ ይቀርፃል። በዛ ውስጥ ሰው ይርብሀል ።ተቃዋሚህ ይበዛል:: እጅ ጠቋሚው ተሳላቂው ይከብሀል:: ብታወራ የሚረዳህ አንዳች አይኖርም!! የሚፈርድ እልፍ ይሆናል...ህመሙ ጥልቅ! የስሜት ጉዳቶቹም ብርቱዎች ናቸው።

ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች ትልቅ ህልም እያላቸው ትንሽ ሆነው መኖርን የሚመርጡት!አስፈሪውም ትልቅ ህልምህ ወደ ትልቅነት የሚመራህ በትናንሽ የህይወት ጉዳዶች ውስጥ መሆኑም ነው። ብቻህን የምታለቅስበት ብቻህን የምትፋለምበት ብቻህን ሞትን ምትናፍቅበት ግን ደግሞ ብቻህን የምትዘምርበት ብቻህን የምትፀልይበት ብቻህን አምላኬ ብለህ ከፈጣሪህ ጋር የምትነጋገርበትም መንገድ ነው።

💡መከራ የፈጣሪ ትህምርት ቤት ነው። "ስቃዮች መገፋቶች መድከሞች መውደቆች  ሁሉም የነፍስ ጥልቅ ህመሞችህ በስተጀርባ መምህሩ አምላክህ አለ።ለዛም ነው ማስተርስ ጫንኩኝ ከሚለው ሰው በተሻለ ህይወት ያስተማረቻቸው አለምን ሲመሩ ሲቆጣጠሩት የትምመለከተው!

''ሰውን ካስተማረው ፈጣሪ በጥበብ አስውቦ የቀረፀው ይበልጣል'' ከሙቀት ጎጆህ ስትወጣ! ህልምህን ከፈጣሪህ ምሪት ጋር ትከተለዋለህ! የግድ ይሆንብሀል አማራጭ ታጣለትህ ብትቀመጥ የሚወጋህ ሺ ስለሚሆን ይግድ ትጓዛለህ እየዛልክ ትጠነክራለህ እየሞትክ ህያው ትሆናለህ እየወረድክ ከፍፍ ትላለህ የግድ ይሆንብሀል...!

📍ህይወት ፊቷን የምምትሰጠው ጠንካራ ጡንቻ ላላቸው ሳይሆን ጠንካራ መንፈስ ላላቸው ነው። ከውስጥ የመነጨ ጠንካራ መንፈስ ሲኖረን ምንም ያህል ችግር ምንም ያህል ስቃይ ከላያችን ቢረበረቡ ምንም ሳያሳስበን
ምንም ተስፋ ሳያስቆርጠን ወደፊት
ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን። ሩጫችንንም መሰናክሉን እያለፍን እንሮጣለን።

💡ወደ ቁልቁለቱም ድፈር! ወደ አስፈሪው መንገድ በድፍረት ጥለቅ ፣ አንድ ሰው መሰረታዊ እሱነቱን በቀጥታ መጋፈጥ አለበት። ለብቻው ሆኖ አይምሮውን በመክፈት ውስጡ ያለውን ነገር መመልከት አለበት። ይህ የድፍረት ተግባር ነው። ከውስጥ ወዳለው ሲዖል ለመግባት የሚያስችል የድፍረት ተግባር....። እርቃን ማንነትን ለመመልከት የሚወሰድ የድፍረት እርምጃ ነው። ታላቅ ድፍረት ያስፈልጋል።

📍የህይወትህን ሲኦል ካልተጋፈጥክ የስኬትህን ብርሀን መቼም አትለብሰውም ፣ የከፍታውን መንገድ በመውርደት ፣ የደስታውን መንገድ በሀዘን ፣ የንግስናን መንገድ በባርነት ፣ የመሪነትን መንገድ በተመሪነት ፣ የስኬትንም መንገድ በውድቀት በኩል ውስጥ ትገናኛቸዋለህ!

አለም ለደፋሮች ታደላለች። ወደ ከፍ ያለ ማንነት ጉዞ ፣ስትጀምር የነፍስክ ጥንካሬ ተአምራዊ ወደ ሆነ ቦታ ያደርሥሀል፣ ድፋር ሁን! ለህልምህ ቆራጥ ሁን ፣ የህይወት ብርሀንህ የሚወለደው ከዛ እርምጃህ ነው!

ዉብ ጊዜን ተመኘን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
የዛሬ ደስታህ የዛሬ ነው። የነገ ደስታህ የነገ ነው። ፈጣሪ አንተን የሚያስደስትህ ነገር ሊሰጥህ ምንም እጥረት የለበትም። አንተ ብቻ በሆነውም ባለህም በሚሆነውም በሁሉም ተደሰት። ውስጥህ የሚያሳምምህን ሳይሆን የሚያስደስትህን እይ። ውስጥህ የሚያሳዝንህን ሳይሆን የሚያዝናናህን እይ።

ውስጤ ያለችውን ትንሽዬ ደስታ አስተውዬ ባየሁ ጊዜ ግን የፈጣሪን መልካምነትና ቸርነት አያለሁ። የፈጣሪን ደግነትና ቅንነት አስተውላለው። ከምንም በላይ የፈጣሪን ፍቅር አያለሁ። በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው ከስምንት ቢሊዮን የዓለም ሰው ሁሉ እኔንም አለመርሳቱ ይደንቀኛል። ውስጤ በፈጣሪ የተቀመጠችውም ትንሽዬ የደስታ ቅባትም በአካሌ ውስጥ ካሉትና በላዬ ላይ ከተፈጠሩት አሉታዊ ነገሮች ሁሉ ትልቃለች።

💡ውስጤ ያለችው ሚጢጢዬ የደስታ ፍንጣቂ ካጋጠሙኝ የሂወት መሰናክሎች ሁሉ ትገዝፍብኛለች። ያኔ ላለመሳቅ ምክንያት አጣለሁ። ከውስጤ የተፈጠረው ደስታ በፊቴ ላይ ይደገማል። መጀመሪያ ውስጤ ይስቃል በመቀጠል ጥርሴ። ከዛ ደሞ የኔ ደስታ ከኔ አልፎ በዙሪያዬ ያሉት ላይ ይጋባና እነሱም ይስቃሉ።

የእውነት ፈጣሪ እንዴት ድንቅ ነው። በሱ ላይ እምነታችንን በጣልን ጊዜ ልባችንን በደስታ ፊታችንን በፈገግታ ይሞላዋል! በእውነት የፈጣሪን ጥበበኝነት መመስከር ከፈለጋችሁ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ውስጠ ውስጣችሁን ተመልከቱ። ያኔ የምታገኙት የደስታ ጨረር ከከበቧችሁ ችግሮች ሁሉ ይበልጡባችኋል። ያኔ ከልባችሁ ትስቃላችሁ።

📍የበለጠ የፈጣሪን የእውቀት ጥግ ደሞ የምታዩት በምንምና በየትኛውም ጊዜ ለእያንዳንዳችን እደግመዋለሁ ለእያንዳንዳችን የሚሆን ደስታ ሰቶናል! እሱ ጋ ስስት የለም። እሱ ጋ ማዳላት የለም። የተወሰኑትን አስደስቶ የተወሰኑትን የሚያስከፋ ሚዛናዊ ያልሆነ አምላክ አይደለም። ውስጣችንን በደንብ ማየት ስንጀምር በገንዘብ ልንገዛው የማንችለውን ደስታ እናገኛለን። ይህም ደስታ ሳቅን ይፈጥርልናል። ጥርሳችንም ከልብ በመነጨ ደስታ ፈገግ ይላል።

💡ዛሬ ይህንን በውስጣችን ያለውን ደስታ የምናይበትና ፊታችንን በሳቅ የምንሞላበት ቀን ነው። አስተውለን ወደ ውስጥ እንይና ውስጣችን ያለውን ደስታ በፊታችን ላይ እንዲንጸባረቅ እንፍቀድለት!ውስጣችንን ስናይና ፈጣሪ ውስጣችን ያስቀመጠውን ድንቅ ስጦታ ስናስተውል ፤ያኔ አለመሳቅ ይከብደናል። አለመደሰት ታሪክ ይሆናል። ከፈገግታችሁ ጀርባ ያሉትን ብዙ ችግሮች መከራዎችና ማጣቶችን ሳይሆን ትንሿን ጥሩ ተአምር እዩ፤ያኔ ትንሿ ብዙ ትሆናለች። ከውስጥ የተጫረችው ሚጢጢዬም የደስታ ፍንጣቂ ከናንተ አልፋ ለዓለም ሁሉ የምትበቃ ትሆናለች።

🔑 ከውስጥህ ያለው ብዙ ነው። ከውስጥሽ ያለው ድንቅ ነው። ፈጣሪንም ለሰጣችሁ ሁሉ አመስግኑ! እውነቴን ነው ውስጠ ውስጣችሁ ያለውን ስታስተውሉ (ማየት ብቻ አይደለም ማየት ወስጥ ማስተዋል ካልተጨመረበት ትርጉም የለውም) ያኔ ባላችሁ ሁሉ ትገረማላችሁ።

ብሩክ የሺጥላ

ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
💡የተለያየ ድርሻ መያዛችን ሕይወትን የተሟላች ያደርጋታል፡፡ ሰዎች እንደ እኛ ካላሰቡ የተሳሳቱ ፣እንደ እኛ ካልተናገሩ ቋንቋ ያበላሹ ፣እንደ እኛ ካልኖሩ የሞቱ እንደ እኛ ካልሰሩ ሥራ የፈቱ አይደሉም ሌሎች አስፈላጊያችን የሚሆኑት እኛ የማንችለውን ሲያውቁና ሲያደርጉ ነው፡፡

📍ሁሉም ሰው ዶክተር ቢሆን ያለገበሬ ምን ይመገባል?? ዶክተሩ በእውቀቱ ተመክቶ ገበሬውን አንተ አታስፈልገኘም ቢለው ይሞኛል እንጂ ምን ይበላል? የላይኛው ከታችኛው የግድ የሚፈላለግበትን ጥምረት ተፈጥሮ ሰጥታናለች ፣ እኛም የድርሻችንን ተሰጦ ተቀብለናል፣ ስለዚህ አንዱ አንዱን አታስፈልገኘም ሊለውና ሕይወትን ብቻውን ሊመራ አይቻለውም፡፡ ትልቁ የኑሮ የኑሮ ሚስጢር " እኔ ለአንተ ፣ አንተ ለእኔ" የሚል ነው፡፡

🔷የጥቁሮች መብት ታጋይ  የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ፡-  አላባማ እያለሁ ጫማዩን የሚጠርግልኝ አንድ ሊስትሮ ነበር፡፡ይህን ሊስትሮ ስመለከት ወደ አእምሮዬ የሚመጣ ነገር ቢኖር የቱንም ያህል ጫማዬን ብጠርገው እንደእርሱ አድርጌ ላሳምረው አለመቻሌ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ ልጅ በጫማ ማሳመር የዶክትሬት ዲግሪ አለው ብዬ ተቀበልኩ፡፡ ከኔም የተሻለ ስለሆነ አከበርኩት" ብሏል፡፡

💡የትኛውም እውቀታችን አዋቂ የሚያሰኘን ላላወቁት በምናደርገው መንገድ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እውነተኛ እውቀት የአገልጋይነት እንጂ የጌትነት መንፈስ የለውምና፡፡ የእኛ እውቀት አስፈላጊ የሚሆነው የማያውቁ ስላሉ ነው፡፡ ሁሉም ቢያውቅ እውቀታቸው አለማወቅ ይሆናል ስለዚህ የማያውቁትን አክብረን ማገልገል ይኖርብናል፡፡

🔷የትኛውም ሀብታችን ባለጠጋ የሚያሰኘን በችግር ለሚያቃስቱት ባፈሰስነው ልክ ነው፡፡ ራሱን የቻለ ባለጠጋ አይባልም፡፡ለሌሎች የተረፈ ግን ባለጠጋ ይባላል፡፡ስኬታችን የሚለካው ራሳችንን በረዳንበት መጠን ሳይሆን በሌሎች በተረፍንበት መጠን ነው፡፡

♦️ዛሬ ኑሮአችንንና ሕይወታችንን እንዲገዛው የፈቀድንለት ነገር ቢኖር ንቀት ነው፣ ሌሎች እንዲያከብሩን እንፈልጋለን ፣ እኛ ግን ሌሎችን መናቅ እንሻለን፡፡ ሌሎችን መናቅ በአዋጅ የተፈቀደልን ሥልጣን ይመስለናል፡፡ ሌሎችን በንቀት ዝቅ ካላደረግን የተስተካከልናቸው አይመስለንም፡፡

💡ስለዚህ የበላይነት ስሜታችን የበታችነት መንፈስ የወለደብን ነው፡፡ የምንኖረው ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም ነውና ሌሎችን...ማክበር ደግሞም ፈጣሪ የምንሰጠውን አስታቅፎ ወደ ዓለም ልኮናልና አደራችንን ማድረስ ይገባናል፡፡

በቤታችን ፣ በሥራ ቦታችን ፣ በአገልግሎታችን እየሰራን ያለን እኛ ብቻ መስሎ ከተሰማን ሌሎች የሠሩት አይታየንም፡፡ ሌሎችን መውደድ ያቅተናል፡፡ ሥራችንም ከጥቅሙ ኩራቱ እየገነነ ይመጣል፡፡ በሌሎች ላይም እምነት እያጣንም የርክክብን ሥርዓት እናፈርሳለን፡፡ ራሳችን አልሚ ሌሎችን አጥፊ ሆነው እየታዩን ነቃፊ ብቻ እንሆናለን፡፡

🔷የዓለማችን ትልቁ የኢኮኖሚ አቅም ፣የሰላም መሰረት ግብረ ገብነት ወይም የሞራል ሕግ ነው፡፡ የሥነምግባር መሰረቱ ሃይማኖት ነውና ሃይማኖትን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡ብዙ ባለ ራዕዯች ነን የሚሉ ሃይማኖትን በቀና መንፈስ አያዩትም፡፡ሃይማኖት ግን የልምድ ሳይሆን የተፈጥሮ መሻት ነው፡፡ መስራት ፣ መማር ፣ መልፋት ፣ መትጋት ብቻውን በቂ አይደለም ሃይማኖት ያስፈልጋል፡፡

♦️ዓለም ድፍርስ ውሃ ናት፡፡ ስለዚህ የጠራ ማንነትን አታሳይህም፡፡ እንደውም እውነትን የምትሸፍን የሽንገላ አዙሪት ውስጥ በመሆኗ ምንም ያልበራለትን የብርሃናት አለቃ፣ አጥፊውን አልሚ ፣ ሰነፉን የትጉሃን አለቃ እያለች ትሾማለች፡፡  የኑሮአችን ባህልም ግለኝነት ባጠቃው "አኔ ለእኔ " በቻ በሚል ራስ ወዳድነት መንፈስ የተከበበ ነው፡፡ ሰዎች መንፈሳዊ መፅሐፍትን የሚጠሉት እውነት ስላልሆነ ሳይሆን ኃጢአጣቸውን ስለሚነግራቸው ነው፡፡ ዛሬ ድረስ የሰው ልጆች ይህን ሀቅ አልተረዱትም አሁንም ሌላውን እንጂ ራሳቸውን ዞር ብለው ማየት አልቻሉም፡፡

🔷ስለዚህ የኛ ድርሻ ቆም ብሎ ማሰብ ነው። ቆም ብሎ ማሰብ ይጠቅማል፣ ቀጥሎ መመልከት ከዚያም መጠየቅ በመጨረሻም መጓዝ ነው፡፡ ካልቆምን መመልከት ፣ ካልተመለከትን ማስተዋል ፣ ካላስተዋልን መጠየቅ ፣ ካልጠየቅንም መጓዝ አንችልም፡፡ መቆም ለቀጣዩ ጊዜ ያዘጋጃል ፣ ለቀጣዩ ጉዞም ኃይል ይሰጣል ፡፡

♦️በክፉ ጎዳና የሚጓዝ መቆም ያስፈልገዋል ፡፡ የመጣበትንና የሚሔድበትን የሚያየው በመቆም ብቻ ነው፡፡ በመቆም በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ራስን መገምገም ፣ ከዚያም መመልከት ቀጥሎም መጠየቅ በመጨረሻም ዕረፍት ወዳለበት የራስ ደሴት መጓዝ፡፡

             ውብ ቅዳሜ❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
📍ወዳጄ ሆይ

ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ። አንተም እንደዛፉ ስር ስደድ ጠንካራነት እውቀት አለው ፣ በጥበብ ይናገራል ፤ ተግባር አለው ። ጠንካራነት ስሜት ሳይሆን ተግባር ፣ ፉከራ ሳይሆን ድርጊት ነው ። ጠንካራነት ሞራልም ምግባርም ነው።

📍ወዳጄ ሆይ

ፊት የልብ አደባባይነውና ሁሉን ቅሬታህን ፊትህ ላይ አታስነብብ፡፡ ጠላቶችህ ፊትህን እንጂ ልብህን እንዲያዩ አትፍቀድ፡፡ ለስድባቸው ስድብን አትመልስ ጆሮ ሰጥቼ ሰምቻችኀለሁ ማለት ነውና፡፡ ለአሳማሚዎችህ በቸኛው ማለፊያ ታምሞ አለመጠበቅ ነው ። ታመህ ካልጠበቀቻው ጆሮ ሰትጠህ ዝቅ ካላልክላቸው የሚያሳምምህ የለምና፡፡ ከራስህ ጋር ሳትመክር ከሰው ጋር አትመካከር፡፡ ለአንድ ሀሳብ የሶስት ቀን እድሜ ስጠው፡፡ ባዕድ ባለበት ስለቤትህ አታውራ፡፡  ለግቢህ አጥር ፣ለቤትህ በር፣ለህይወትህ ሚስጥር ይኑርህ፡፡ የተሻልክ ሳይሆን የበለጥክ ሁን፡፡

📍ወዳጄ ሆይ

መሬትህ በሚሸከመው መጠን ቤትህን ሥራ ፣ ወዳጅህ በሚችለው መጠን ምሥጢር ንገረው ፣ ተማሪህ ባደገበት መጠን መግበው ። የሌላው የሆነችውን ሴት ላንተ አትመኝ ። ያንን ጥላ ስትመጣ አንተን ጥላህ መሄድ እንደምትችል እያስተማርካት ነው ። አንቺም የሌላውን ባለትዳር አትመኚ ።

📍ወዳጄ ሆይ

ብትታመም በአገርህ ትታመማለህ ። አገርህ የታመመች ከሆነች ግን ዓለም ዝግ ይሆንብሃል ። ተሰደህም ለመከበር አገር ያስፈልግሃል ። ከሰላም የበለጠ ሀብት ፣ ከማስተዋል የበለጠ ሥልጣኔ ፣ ከፍቅር የበለጠ ደስታ የለም ። ያለ ፈጣሪ እየተስፋፉ ያሉ ሰዎች እየጠበቡ ነው ። ልብስ ጸድቶ ልብ ከቆሸሸ የመንፈስ ነጻነት ገና አልመጣም ። የድሮ ሰው ልቡ ንጹሕ ፣ ልብሱ አዳፋ ነበር ። የዛሬ ልጅ ልብሱ ንጹሕ ፣ ልቡ ሸርታታ ነው።

📍ወዳጄ ሆይ

የሰብዊነት ሥራ ለሰው ሁሉ የሚደረግ የደግነት ስራ ነው፣ ደግ ለመሆን ጥግ አትያዝ ። ከሥርህ ያለው አንተ የማትችለውን የሚችልልህ ነውና አክብረው ። ቆጥረህ ከሰጠህ ስጦታህ ይረክሳል ። ደብቀህ ከሰጠህ ስጦታህ ሲወራ ይኖራል ። ከፍ ስትል ልታይ ካልክ ሁሉም ሰው ስትወድቅ ያይሃል ። በከፈትክለት መጠን ጠላት ይገባል ። ሰይጣን አስገድዶ ሳይሆን አዘናግቶ የሚገድል ጠላት ነው ።

💡እናም ወዳጄ

የታወከ ሌሊት ሲገጥምህ በሰላም ስላደርክባቸው ሌሊቶች አለማመስገንህን አስብ ። ቀኑ መብትህ ሳይሆን ስጦታህ ነውና አመስግንበት ። እሰይ ነጋ ማለት ሲገባህ ደሞ ነጋ አትበል ።ሲያነጋልህ ምንም ክፈያ ላላስከፈለህ ጌታ የማለዳ ምስጋና ለማቅረብ አትዘግይ ። ወጥቶ የመግባት ዋጋው ትልቅ ነውና የምሽት ጸሎትህንም አታስታጉል ። እያጣጣርክ ስለ ጤና ከመጸለይ በጤናህ ፈጣሪህን አመስግን ።

ውብ ጊዜ❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
💡ስሙኒ ይቀራል

📍ከአንድ ሰው በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ ድንች የሚሸጥ ምሲኪን ሰው ነበረ። የቤቱ ባለቤት ሁሌም ወደ ውጪ ሲወጣ ይህንን ምስኪን ሰው ይመለከተው ነበረ። ቀኑን ሙሉ ብርድና ጸሀይ እየተፈራረቀበት ኑሮን ለማሸነፍ መድከሙ ስላሳዘነው በአቅሙ ሊረዳው ወሰነ።

💡ነጋዴው አንዷን ድንች በ50 ሳንቲም ነበር የሚቸረችረው። ታዲያ ይህ ሰው ምስኪኑን ነጋዴ ለመርዳት በማሰብ በየቀኑ የአንድ ድንች ዋጋ እየሰጠው ለመሄድ ወሰነ። በየቀኑ 50 ሳንቲሙን እየሰጠው በአንጻሩ ምንም ድንች ሳይቀበል ይሄዳል። ከብዙ ጊዜ በኋላ ይህ ሰው እንደለመደው 50 ሳንቲሙን አኑሮለት ጉዞውን ቀጠለ።

ድንገት ከኋላው “ጌታዬ” የሚል ጥሪ ይሰማል። ዞር ብሎ ሲመለከት ምስኪኑ ነጋዴ ነበር በሩጫ የደረሰበትና የጠራው።

ሰውየው በፈገግታ “ከስንት ጊዜ በኋላ ለምን በቀን በቀን 50 ሳንቲም በነጻ እየሰጠሁ እንደማልፍ ልጠይቀኝ ነው ያስቆምከኝ?” አለው

ነጋዴው ግን እያለከለከ “አይደለም ኸረ” ሲል መለሰ። ይሄኔ ሰውየው ግራ ገብቶት

“እና ለምን አስቆምከኝ?” ቢለው

“የድንች ዋጋ 75 መግባቱን ልነግርዎት ነው፤ እናም ስሙኒ ይጎድላል” አለው አሉ።

💡ይህንን ታሪክ የሰማሁኝ ቀን በጣም አስቆኝ ነበር። መለስ ብዬ ሳስበው ግን ከቀልድነቱ በላይ የሰው ልጅን የአልጠግብ ባይነትና ያለማመስገንን ባህሪ የሚያንጸባርቅ መስሎ ታየኝ። ሰዎች አመስጋኝ ፍጡሮች ነን ብዬ አላምንም። ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነጻ በሚሰጠን ነገር ላይ እንኳን እንደራደራለን። የእኛ ባልሆነው ሀብት እንሟገታለን። በቸርነት በተሰጠን ነገር ሁሉ ይበልጥ እንጠይቃለን። ሃምሳ ሳንቲም ለምን በነጻ ተሰጠኝ ሳይሆን ለምን ስሙኒ ጎደለ የሚል አመለካከት ስላለን እኮ ነው አብዛኛዎቻችን ባለን ነገር መደሰት የሚያቅተን።

📍ብዙ ጊዜ ከፈጣሪ ጋርም ሆነ በየእለት ኑሮዋችን በነገሮች ላይ የምንደራደረው ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነው። በነጻ የሚሰጠንን 50 ሳንቲም ሳይሆን የኑሮዋችንን ዋጋ እራሳችን ተምነን ቀሪው ጎደለ ብለን እንሟገታለን። ስዎች የሚሰጡንን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት ዋጋ የማንሰጠው ቀሪውን ስሙኒ ስለምናስብ ነው።እኛ በባህሪያችን ነጻ የሆነን ነገር ዋጋ አንሰጠውም፣ የሚያስደንቀው ግን የሰው ልጅ በምንም ያህል ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችላቸው ሀብቶቹ በሙሉ በነጻ የሚያገኛቸው ናቸው።

💡በ50 ሳንቲሙ ያልተደሰተና ያላመሰገነ ሰው ስሙኒ ቢጨመርለት ምን ዋጋ አለው? በየቀኑ የሚቸረን 50 ሳንቲም ከበቂ በላይ ነው፤ አንዳንዴ ስሙኒው ይቀራል ብለን ሰጪውን ባናስቀይም መልካም ነበር፤ ነገር ግን ሰው ነን!!! ብዙ ጊዜ ደስታችንን የሚነጥቀን የ “ስሙኒ ይቀራል” አይነት አመለካከታችን ነው። የተሰጠንስ 50 ሳንቲም? የተሰጠን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት፤ ነጻ ጤንነት፤ ነጻ ተስፋ? ከምንም በላይ ነጻ ህይወትስ?

ሚስጥረ አደራው

ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
💚ከትሕትና የበለጠ መልካም ነገር የለም። የደካማነት መገለጫ አይደለም ፣ ትህትና የትንሽነት ምልክት አይምሰልህ ፣ የዋህነት ደካማነት ሳይሆን የለስስት የመኖር ችሎታ ነው፣ ደግነት የመልካም ሰው የህይወት መምርያ ነው። ትህትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው፡፡ ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ቀና የሚሉት ፍሬ የሌላቸው ናቸው፡፡ትህትና የልብ ነው፡፡

አየህ አንተ ባታስበውም አንተ የምታስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ ፣ ያንተ መኖር የሚያኖራቸው አያሌ ሰዎች አሉ ። ህይወትም ትርጉሟ የሚጨምረው ለሌሎች መኖር ስንጀምር ነው፣ ምንም የለኘም ምንም መስጠት አልችልም አትበል ያለህን ካሰብከው ብዙ ነገር ማድረግ ትችላለህ፡፡

💛"ሰው ሁሉ በልቡ ያለውን ይሰጣል።"
በውስጥህ ያለውን ነው የምትሰጠው ፣ ሁሌም ደግ ሁን። ቸር ለመሆን ሃብት እስክታገኝ አትጠብቅ። አንዳንዶች ካንተ የሚፈልጉት ፈገግታህን ነው ፤ አንዳንዶች ሰላምታህን ፤ አንዳንዶች ጊዜህን ፤ አንዳንዶች ሃሳብህን ፤ አንዳንዶች ድጋፍህን ፤ አንዳንዶች ጓደኝነትህን ሊሆን ይችላል ።

❤️ሁላችንም ለሌላው የምናካፍለው ብዙ ነገሮች አሉን ፈገግታ እና ደስታችን እንኳን የምናውቀውን ሰው ቀረቶ የመንገደኛውን ሰው ቀን ብሩህ የማድረግ ሃይል አላቸው። ሀብታም ሁን ወይም ደሀ ደግነትህን በዛ ሚዛን አትመዝነው! ዋናው የሚያስፈልግህ ሀብታም የሆነ  ልብ ብቻ ነው"!

              ውብ አዳር ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
📍ምን ይዤ ልሔድ ልድከም?

ታላቁ እስክንድር እንዲህ አደረገ አሉ። ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ፤ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው "ስትቀብሩኝ፤ እጄን ወደ ላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ" አለ። ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት፤ እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ "እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት፤ ስሞት ከምድር ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው " አለ ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው። በክንዱ ስንቱን ያስገበረው ታላቅ፤ "ምንም ይዤ አልሄድም" ሲል ተናገረ። አንዳንዴ የምንኖረው እስከመቼ ነው ብለን እራሳችንን ከምር ብንጠይቅ መልሱ ያስደነግጠናል።

💡 ምክንያቱም የምንጨነቀው ከምንኖረው በላይ ነው። ፈገግታን፤ ሳቅን፤ ደስታን ሳያውቁ የሚሞቱ ሰዎች ሞልተዋል። ኖረው ሳይሆን፤ ሞተው ወደ መቃብር የሚወርዱ ምስኪኖች ብዙ ናቸው። አብዛኛዏቻችን በቁማችን ሞተናል፤ ምክንያቱም መኖር ከመንቀሳቀስ እና ከመተንፈስ የጠለቀ ስሜት አለውና። መኖር ማለት እራስን ከአሁኗ ደቂቃ ጋር አጣምሮ፤ መንፈስን፤ አይምሮን ከተፈጥሮ ጋር አዋህዶ፤ ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው የሚለውን የጠቢቡን መርህ ተከትሎ ህይወትን መምራት ማለት ነው (በጥቂቱ)።

ይህ ትርጉም ለእያንዳንዳችን በልካችን መበጀት ይችላል። አንዳንዴ እራሴን እጠይቃለው፤ የምንጨነቅለት ነገር ሁሉ ከዚህ አለም ስንሄድ ይዘነው የምንሄደው ካልሆነ፤ ምንድን ነው ነጥቡ? የብዙዏቻችን ኑሮ ይዘነው ለማንሄድ ወይም ስማችንን ከመቃብር በላይ ለማያስጠራ፤ ተራ ነገር ተሰውቷል። የቱ መቅደም እንዳለበት አናውቅም፤ እኛ ወይስ ጭንቀታችን? ቤተሰባችን ወይስ ስራችን? ሰብዓዊነት ወይስ ቁሳዊነት?

♦️ተጨንቀን የምናጠራቅመው ገንዘብ፤ በጥላቻ የገነባነው ክብር፤ በደም ያገኘነው ስልጣን፤ በስርቆት ያካበትነው ሃብት፤ በውሸት የፈጠርነው ማንነት፤ ሁሉም ስንሞት አብረውን አይሄዱም። ያንን ማስተዋል እንዴት አቃተን? በቃ ሃቁ ይህ ነው፤ ምንም ነገር ከኛ ጋር ወደ መቃብር አብሮ አይወርድም።

💡ይህንን ሳስብ ግርምት ያዘኝ፤ እንዴት እናሳዝናለን ? ምን አልባት ስዎች ሲቀበሩ እጃቸውን ወደላይ አድርገው ቢሆን ኖሮ፤ በጥቂቱም ቢሆን ህይወታችንን እንዴት መኖር እንዳለብን ትምህርት ይሆነን ነበር። በህይውትህ የሚያስጨንቅህ ነገር ሲገጥምህ፤ እስከምን ድረስ እራስህን አሳልፈህ መስጠት እንዳለብህ ለማውቅ ሞክር፤ ምናልባት ከህይወትህ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ሊሆን ይችላልና።

አቤል ብርሀኑ

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
📍የተሻለ አለህ

በአውሎ ንፋስ ውስጥ ብትሆን፣ ዶፍ ዝናብ ቢወርድብህ፣ ዋጋህ ያነሰበት፣ መኖርህ የማይቆጠርበት፣ አበርክቶትህ የማይታይበት፣ ስራህ የማያፈራበት፣ ማንነትህ የማይመረጥበት ስፍራ ብትኖር እንኳን ፈጣሪ አብሮህ ካለ ሁሌም የተሻለ ከፍ ያለ ነገር አለህ።

🔷ምንም እንኳን እምነታችን ቢጎድል፣ ክፋታችን ቢበዛ፣ ሃሳባችን ቢያንስ፣ ምግባራችን የወረደ፣ ስራችንም አሳዛኝ ቢሆንም ፈጣሪ ግን ጥሎ አይጥለንም።፣ ትቶ አይተወንም ሁሌም ይመለከተናልና መቼም ችላ አይለንም። የተውን ሰዎች ይኖራሉ፣ ያገለሉን፣ የተጠየፉን እንዲሁ እንደዋዛም የናቁን ሰዎች ይኖራሉ ዋናው ነገር ግን በፈጠረን አለመገፋታችን አለመረሳታችን ነው።

♦️የተሻለ አለህ! ከዛሬው የላቀ፣ ከትናንት የገዘፈ፣ ከአሁንህ ያየለና ከፍ ያለ ስፍራ ይኖርሃል። የማይቀየሩ የሚመስሉ ከባድ ሁኔታዎች ይቀየራሉ፤ ይወርዱ የማይመስሉ ሸክሞች፣ ይፈቱ ያልመሰሉ ችግሮች፣ ይስተካከሉ ያልመሰሉ ውጥንቅጦች ይወርዳሉ፣ ይፈታሉ፣ ይስተካከሉ።

እምነትህ ቢፈተን ግራ አትጋባ ይልቅ ለተሻለ ክብር እንደታጨህ አስተውል፤ በፈተናህ ብዛት አትደናገር ይልቅ የድልህ ቀን ቅርብ እንደሆነ አስተውል። በጫናዎች ብዛት የማትሸበር፣ ለምድራዊ ፈተና የማትበገር፣ ከፈጣሪህ ውጪ እንዳልሆንክ አስተውል።

🔷አንዳንዴ ማሳለፍ እየቻልን አቅፈናቸው የምንቀጥላቸው ብዙ ኮተቶቻችን ጣእሙን ማየት እንዳንችል ሁሉ ነገራችንን ዘግተንባቸዋል። ለማማረር እንጂ ለማመስገን ስንፈናል ለማዘን እንጂ ለመደሰት ጉልበት አጠተናል። መቆየት በማይገባን ቦታ ላይ በመቆማችን ማሳለፍ የሚገባንን አላፊ ሃሳቦችን እንዳያልፋ መንገድ ዘግተንባቸዋል እሰኪ ነቅነቅ እንበል እናሳልፋቸው የሚመጡት ሁሉ እንደአመጣጣቸው እንሸኛቸው አኛም ከቆምንበት አስተሳሰብ ስናልፍ ሁሉም ጊዜያዊ መሆኑን እናውቃለን።

ሁሉም ያልፍ የለ ትላንትናም አልፏል ዘሬም ታልፋለች ነገም ትቀጥላለች እኔም አንተም እናልፋለን ምክንያቱም ሁሉም ያልፋል።ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን የያዘ፣ በሁሉ ውስጥ ያለው አምላክህ ባንተ ውስጥ ስለመኖሩ አትጠራጠር፤ ለተሻለው ስፍራ እንደሚያበቃህ እምነት ይኑርህ።

🔑ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል።

ውብ አሁን ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💎እንደ ንስር ወደ ላይ ከፍ በል

ወዳጄ ንስር ሁን በቀቀንነት ይቀርብህ። በቀቀን የሌሎችን ሰዎች ሕይወት በመመሰል ውድድር ከፍ ብሎ መብረር አይችልም። ስጦታውን፣ እውቀቱን እና ክህሎቱን ከማዳበር ይልቅ ሌሎችን መስሎ መኖር ይመቸዋል።

ሕይወት ደግሞ በተቃራኒው ከበቀቀኖች ይልቅ ለንስሮች ፍሬዋን ትሰጣለች። ተፈጥሮ ብዙ ቀለም ፣ ብዙ ዕድል፣ ብዙ ፈተና ናት። ንስር አሞራ የለውጥ ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው በስራ የዳበረ ከእውነተኛው ዓላም ጋር የተሰናሰለ ስብእና ስለገነባ ነው።

📍ንስር የአእዋፋት ሁሉ ንጉስ ነው ሲባል በዋዛ እንዳይመስላችሁ። ንስር የሃይል ሚዛኑን ለመጠበቅ በቂ የሆነ ልምምድ የሚያደረግ ፣ የሚፈልገውን ነገር ከማድረግ  የማይቆጠብ ቁርጠኛ የስነ ልቦና ተምሳሌት ነው ። ህይወቱን ሙሉ ትኩስ ስጋ እያደነ ነው የሚኖረው ። የሞተ ነገር አይነካም። የእለት ሲሳዩን እያደነ ይበላል እንጅ እንደ ቁራ የሞተ በክት እያሸተተ አይቀላውጥም። ሃይሉን እያደሰ የእንደገና ድልና ስኬቱን እያጣጣመ በንግስናው እስከወዲያኛው ይዘልቃል።

ሰማዩ ሲጠቁር ደማናው ወጀቡንም ሲያይል ሌሎች እዕዋፋት በየ አለቱና በየጥሻው ችፍርግ ወስጥ ይደበቃሉ በቤት ታዛ ስርም ይደበቃሉ። ንስር ግን ደስ ይለዋል ወጀቡ ሲጀምር ንፋሱን በመሞገት የራሱን ጥንካሬ ይላካበታል።  የነፋሱን አቀጣጫ በመከተልም ይበራል። ረሱን ወደላይ ለማምጠቅና የከፍታውን ጫፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል ፣ በዚህም ጥንካሬውን ይለካበታል።

💎ንስር ወጀብ ከመምጣቱ ብዙ አስቀድሞ ማወቅ ይችላል። እንዳወቀም ከፍታ ቦታ ለይ ይቀመጥና ንፋሱን ይጠብቃል። ወጀቡ ሲመጣ ከተቀመጠበት በመብረር ንፋሱ አግዞት ከወጀቡ በላይ እንዲበር ያደርገዋል። ወጀቡ ከታች ያለውን ዓለም ሲያተራምሰው፣ ንስሩ ከወጀቡ በላይ ይንሳፈፋል። እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ እንበል። ንስሩ ወጀቡን አላመለጠውም ፤ ተጠቀመበት እንጂ !!

📍የሕይወት ወጀብ ወደ እኛ ሲመጣ፣ ልክ እንደ ንስሩ ከወጀቡ በላይ መብረር እንችላለን፤ በሽታን፣ አደጋን፣ ውድቀትን፣ እና ሃዘንን ወደ ሕይወታችን የሚያመጣውን ንፋስ ለከፍታችን መወጣጫ ልናደርገውው እንችላለን።

🔑እናም ወዳጄ

አንተም መከራንና ፈተናን አትፍራ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥም ቢሆን መንገድ አለና መከራውን ግብግቡን የአዳዲስ ሐሳቦች መነሻ የጥናካሬህ መለኪያ አቅምህን የምትጠቀምበት አጋጣሚ፣ አልፎም ወደ ላይ የምትመጥቅበትና ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት ዕድል አድርገው። እንደ ሌሎች ወፎች ከመከራው አትሽሽ ከችግሩንም አትደበቅ መከራን ለጥንካሬና ለበረከት ተጠቀምበት።

          ውብ የስኬት ጊዜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌗በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል ስንት ወርቅ ይዛችሁ እንደመዳብ ካቀለላችሁት ከእጃችሁ ሲወጣ ይቆጫችኋል። ዛሬ እናታችሁ አጠገባችሁ ስላለች አመስግኑ ዛሬ አባታችሁ ስላለ ተመስገን በሉ ዛሬ ጤና ስላላችሁ ፣ ዛሬ ወጥታችሁ መግባት ስለምትችሉ አመስግኑ።

💡ይህ ሁሉ ባይኖራቸሁ እንኳን በህይወት ስላላችሁ ተመስገን በሉ፣ በህይወት ያለ ነውና የተበላሸውን ማስተካከል የሚችለው። በህይወት ከመኖር በላይ ዋጋ ያለው ነገር የለም፤ የምናገኘውም የምናጣውም በህይወት ስላለን ነው። መኖርን ደግሞ በነፃ ነው ያገኘነው፣ ምሬት ዓይንን ያጨልማልና ደስተኛና አመስጋኝ እንሁን።

💡እጅግ ውድ የሆኑ ነገሮች በነፃ ነው የተሰጡን፡፡ ፈጣሪ የአቅማችንን ልክ ስለሚያውቅ የከበሩትን ነገሮች ያለክፍያ አስረከበን፡፡ አየር፣ውሀ፣ ደማችን፣ አካላችን፣ ፀሀይዋ፣ ዝናቡ እና አፈሩ በክፍያ ቢሆኑ ማን መግዛት ይችል ነበር? ህልውናችን በነኝህ ነገሮች እጅግ የመቆራኘቱን ያህል በገንዘብ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ እኔነኝ ያለ የምድር ባለጠጋስ ወጪውን ይችለው ነበር ወይ ?

❤️በነፃ የተሰጡን ባይኖሩ ኖሮ ሰው በውድ የሚራኮትባቸው ቁሶችስ መች ይኖሩ ነበር፡፡ ሰው ርካሹን በውድ ይሸጣል ፈጣሪ ግን ውዱን በነፃ ይሰጣል፣ ማጉረምረሙን ትተን ስለ ፈጣሪ ለጋስነት እናመስግን ከምናስበው በላይ ባለፀጎች ነን፡፡

🌗ስለ ሁሉ ነገር አመስጋኝ ሁን ማመስገን ስትጀምር አለም ወደአንተ ታዘነብላለች ነገሮች በሙሉ መልካም ይሆናሉ። ካሰብከው በላይ ሁሉ ነገር ሲስተካከል ሲያምር ታየዋለህ በምድር ላይ ሁሉ ነገር ለመልካም እንደሆነ ስታውቅ፣በማመስገን ስትታጀብ ቤትህም ይደምቃል ኑሮህም ይሞቃል በረከት ሁሉ ወዳንተ ይመጣል።

ልባችን ሁሌም ለምስጋና ክፍት ይሁን!

         ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ጨለማው ላይ ብታፈጥ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።ፈጣሪህን ትተህ በመከራህ ላይ ብታፈጥ አንዳች ጥቅም የለውም። ካስተዋልከው ጨለማም ውበት አለው። ከካባ ይልቅ ደማቅ ነው። እሾህም አበባ አለው። ክፉ ሰውም አንድ ጥሩ ነገር አለው። ልብ አድርግ ለክረምት በጋ፤ ለሌሊት ቀን አለው። ላንተም ጊዜ አለህ። ጊዜን የሚሰጥ ራሱ ጊዜ ሳይሆን የጊዜ ባለቤት ፈጣሪ እንደሆነ እመንና ጠብቅ።

ጊዜ ለታጋሾች የማታሳየው የለም። መስበርም መጠገንም ትችላለች ፣ አንተርሳ ትዘቀዝቃለች ፣ ዘቅዝቃ ታቃናለች። ለጊዜ የሚሳናት የለም፣ እንዳወጣች ታወርዳለች ። አንተም በፈታኝ ጊዝያቶች ክብርህን ጠብቅ። ፈተና ውስጥ እንኳ ብትሆን የሥሜት ብስለትህን እና ራስ ገዝነትህን አሳይ። ታጋሽ፣ ፅኑ፣ ተረጂ ለመሆን እንዳትዘነጋ።

📍እንደ እንስት ውበት ያጌጠው  ህይወታችን ፣ ቀን ሲገፋ ይደበዝዛል እስከተፈቀደልን አብርተን ጊዜ ሲቋጭ ጭልመት እንላበሳለን። አጥቶ ማግኘት እንዳለው አግኝቶ ማጣት አለ ፣ ብርሀኑ ቢጨልም አንከፋ ለበጎ ነው፣ ጭልመት በብርሃን ሲቀየር አንገረም። ምንም ዘላለም ሊቆይ አልመጣም።

ተስፋ ከቤታችን አይጥፋ!
             ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
2024/04/27 18:31:48
Back to Top
HTML Embed Code: